ወደ አንተ እንዳይቀርቡ በልባብና በልጓም ጉንጫቸውን እንደሚለጕሙአቸው፥ ልብ እንደሌላቸው እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ አትሁኑ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በመከራ ውስጥ ነኝና ማረኝ፤ ዐይኖቼ በሐዘን ደክመዋል፤ ነፍስና ሥጋዬም ዝለዋል።
በጠላቴ እጅ አልዘጋኸኝም፥ በሰፊም ስፍራ እግሮቼን አቆምህ።
እግዚአብሔር ሆይ! በችግር ላይ ስለ ሆንኩ ምሕረትን አድርግልኝ፤ ዐይኖቼ፥ ነፍሴና ሥጋዬ በሐዘን ደክመዋል።
ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።
ዐይኖች ከእንባ የተነሣ ፈዘዙ፥ ሁሉም እጅግ ተጸየፉኝ።
ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል? ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?
ዐይኔ ከቍጣ የተነሣ ታወከች፤ ከጠላቶቼ ሁሉ የተነሣ አረጀሁ።
አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሕዝብም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።
የባሕርን ኀይል አንተ ትገዛለህ፥ የሞገዱንም መናወጥ አንተ ዝም ታሰኘዋለህ።
ፌ። በማያድን ወገን እያመንን ረዳታችን ከንቱ ስለ ሆነ፥ እኛ ገና በሕይወት ሳለን ዐይኖቻችን ጠፉ።
ስለዚህ ልባችን ታምሞአል፤ ስለዚህም ነገር ዐይናችን ፈዝዞአል፤