ኀጢአታቸው የተተወላቸው፥ በደላቸውንም ሁሉ ያልቈጠረባቸው ብፁዓን ናቸው።
እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተን መጠጊያ አደረግሁ፤ ከቶም አልፈር፤ በጽድቅህም ታደገኝ።
ለመዘምራን አለቃ፥ በማድነቅ ጊዜ፥ የዳዊት መዝሙር።
እግዚአብሔር ሆይ! መጠጊያ እንድትሆነኝ ወደ አንተ መጥቻለሁ፤ ስለዚህ እንዳፍር አታድርገኝ፤ በጽድቅህም አድነኝ።
ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፈትን።
አቤቱ፥ በጆሮአችን ሰማን፥ አባቶቻችንም በዘመናቸው በቀድሞ ዘመን የሠራኸውን ሥራ ነገሩን።
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
መጽሐፍ፥ “የሚያምንበት ሁሉ አያፍርም” ብሎአል።
ተስፋም አያሳፍርም፤ በሰጠን በመንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሔር ፍቅር በልባችን መልቶአልና።