ሕይወቴ በመከራ አልቋልና፥ ዘመኔም በጩኸት፤ ኀይሌ በችግር ደከመ፥ አጥንቶቼም ሁሉ ተነዋወጡ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ስማ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ ረዳት ሁነኝ።”
ወደ ጉድጓድ ብወርድ ከደሜ ምን ጥቅም ይገኛል? አፈር ያመሰግንሃልን? እውነትህንም ይናገራልን?
እግዚአብሔር ሆይ! ስማኝ፤ ማረኝም፤ እግዚአብሔር ሆይ! እርዳኝ።
ለእጆቼ ጠብን፥ ለጣቶቼም ሰልፍን ያስተማራቸው አምላኬ እግዚአብሔር ይመስገን፤
እግዚአብሔር ረዳቴና መታመኛዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ፥ እርሱም ይረዳኛል፤ ሥጋዬም ለመለመ፥ ፈቅጄም አምነዋለሁ።
የእግዚአብሔር ቃል የእሳቱን ነበልባል ይቈርጣል።
ልቤ በላዬ ደነገጠብኝ፥ የሞት ድንጋጤም መጣብኝ።
በጭንቀቴ ደክሜአለሁ፤ ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፥ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ።