ከሚከብቡኝና በእኔ ላይ ከሚነሡ ከአእላፍ አሕዛብ አልፈራም።
በየአቅጣጫው የከበበኝን፣ አእላፍ ሕዝብ አልፈራም።
እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፥ ጌታም ደግፎኛልና ነቃሁ።
በዙሪያዬ የከበቡኝን በብዙ ሺህ የሚቈጠሩትን ጠላቶቼን አልፈራቸውም።
በዚያም የእስራኤል ሕዝብ በዳዊት አገልጋዮች ፊት ወደቁ፤ በዚያም ቀን ታላቅ ውጊያ በዚያ ሆነ፤ ሃያ ሺህ ሰዎችም ሞቱ።
የምድር ነገሥታት ተነሡ፥ አለቆችም በእግዚአብሔርና በመሲሑ ላይ እንዲህ ሲሉ በአንድነት ተሰበሰቡ።
ልቡ ንጹሕ የሆነ፥ እጆቹም የነጹ፥ በነፍሱ ላይ ከንቱን ያልወሰደ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ።
እግዚአብሔር ልዑል፥ ግሩምም ነውና፥ በምድር ሁሉ ላይም ታላቅ ንጉሥ ነውና።
እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማስተዋል ዘምሩ፤
በተቀመጥህም ጊዜ አትፈራም፤ ብትተኛም መልካም እንቅልፍ ትተኛለህ።
ስትሄድም ይመራሃል፤ ከአንተም ጋር ይኖር ዘንድ ውሰደው። ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣም ያነጋግርሃል።
እንግዲህ ስለዚህ ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእና ጋር ከሆነ ማን ይችለናል?