አንተ በሰማይ ስማ፤ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የባሪያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለሕዝብህም ርስት አድርገህ ለሰጠሃት ምድር ዝናብን ስጥ።
መዝሙር 25:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥ ከዐመፀኞችም ጋር አልገባሁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፈለግህንም አስተምረኝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ዱካህን እንዳውቅ አድርገኝ፤ መንገድህንም አስተምረኝ። |
አንተ በሰማይ ስማ፤ የሚሄዱበትንም መልካም መንገድ በማሳየት የባሪያዎችህንና የሕዝብህን የእስራኤልን ኀጢአት ይቅር በል፤ ለሕዝብህም ርስት አድርገህ ለሰጠሃት ምድር ዝናብን ስጥ።
አሁንም በፊትህ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆነ፥ ዐውቅህ ዘንድ በፊትህም ሞገስን አገኝ ዘንድ ይህም ትልቅ ሕዝብ ሕዝብህ እንደ ሆነ ዐውቅ ዘንድ ተገለጥልኝ” አለው።
ሕግ ከጽዮን፥ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና ብዙዎች አሕዛብ መጥተው፥ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፥ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱም መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን” ይላሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፤ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች ዕወቁ፤ በእርስዋም ላይ ሂዱ፤ ለነፍሳችሁም መድኀኒትን ታገኛላችሁ፤” እነርሱ ግን፥ “አንሄድባትም” አሉ።