የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
መዝሙር 24:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የልጅነቴን ኀጢአትና ስንፍናየን አታስብብኝ። አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት፥ እንደ ምሕረትህ ዐስበኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተ ደጆች፤ ቀና በሉ፤ እናንተ የዘላለም በሮች፤ የክብር ንጉሥ እንዲገባ ብድግ በሉ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንት በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፥ የዘለዓለም ደጆችም ተከፈቱ፥ የክብርም ንጉሥ ይግባ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በሮች ራሳችሁን ከፍ አድርጉ፤ የክብር ንጉሥ ይገባ ዘንድ እናንተ ጥንታውያን በሮች ተከፈቱ። |
የእግዚአብሔርንም ታቦት አምጥተው ዳዊት በተከለላት ድንኳን ውስጥ በስፍራዋ አኖሩአት፤ ዳዊትም የሚቃጠልና የሰላም መሥዋዕትን በእግዚአብሔር ፊት አሳረገ።
ካህናቱም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት በቤቱ በቅድስተ ቅዱሳን ውስጥ ከኪሩቤል ክንፍ በታች ወደ ነበረው ወደ ስፍራዋ አገቧት።
አንተም የመንጋ ግንብ ሆይ፥ የጽዮን ሴት ልጅ አምባ፥ ወደ አንተ ትመጣለች፥ የቀደመችው ግዛት፥ የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ መንግሥት ትደርሳለች።
ከፊተኛው ይልቅ የዚህ የሁለተኛው ቤት ክብር ይበልጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ በዚህም ስፍራ ሰላምን እሰጣለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ነገር ግን በጌታችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና እውቀት እደጉ። ለእርሱ አሁንም እስከ ዘላለምም ቀን ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።