መዝሙር 24:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩምና። በከንቱ የሚበድሉ ሁሉ ዘወትር ይፈሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ሊወጣ ይችላል? በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ጌታ ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል፤ በተቀደሰ ስፍራውስ ማን ይቆማል። |
እግዚአብሔርም እንዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! ልብ አድርግ፤ ስለ እግዚአብሔርም ቤት ሥርዐትና ሕግ ሁሉ የምነግርህን ሁሉ በዐይንህ ተመልከት፤ በጆሮህም ስማ፤ የቤቱንም መግቢያ፥ የመቅደሱንም መውጫ ሁሉ ልብ አድርግ።
ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በእስራኤል ልጆች መካከል ከአሉት ሁሉ በልቡና በሥጋው ያልተገረዘ የባዕድ ልጅ እንግዳ ሁሉ ወደ መቅደሴ አይግባ።
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
እነሆ፥ መልእክተኛዬን እልካለሁ፥ መንገድንም በፊቴ ያስተካክላል፣ እናንተም የምትፈልጉት ጌታ በድንገት ወደ መቅደሱ ይመጣል፣ የምትወዱትም የቃል ኪዳን መልእክተኛ፥ እነሆ፥ ይመጣል፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ስምዖን ጴጥሮስም፥ “ጌታ ሆይ፥ ወዴት ትሄዳለህ?” አለው፤ ጌታችን ኢየሱስም መልሶ፥ “ወደምሄድበት አሁን ልትከተለኝ አትችልም፤ ኋላ ግን ትከተለኛለህ” አለው።
ጌታችን ኢየሱስም፥ “አትንኪኝ፤ ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና፤ ነገር ግን ወደ ወንድሞች ሂጂና፦ ወደ አባቴ፥ ወደ አባታችሁ ወደ አምላኬ፥ ወደ አምላካችሁም አርጋለሁ አለ ብለሽ ንገሪአቸው” አላት።
ስለዚህ የማይናወጥ መንግሥትን ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሀት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ።