ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
መዝሙር 2:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፤ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እናንተ ነገሥታት ልብ በሉ፤ እናንተ የምድር ገዦችም፣ ተጠንቀቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም እናንት ነገሥታት፥ ልብ አድርጉ፥ እናንት የምድር ፈራጆችም፥ ተገሠጹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ነገሥታት አስተውሉ፤ እናንተ የምድር ገዢዎች ተጠንቀቁ። |
ነገሥታትም አሳዳጊዎች አባቶችሽ ይሆናሉ፤ እቴጌዎቻቸውም ሞግዚቶችሽ ይሆናሉ፤ ግንባራቸውንም ወደ ምድር ዝቅ አድርገው ይሰግዱልሻል፤ የእግርሽንም ትቢያ ይልሳሉ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቂያለሽ፤ እኔንም በመተማመን የሚጠባበቁ አያፍሩም።”
ብዙዎች አሕዛብ እርሱን ያደንቃሉ፤ ነገሥታትም አፋቸውን ይዘጋሉ፤ ስለ እርሱ ያልተወራላቸው ያውቁታልና፥ ያልሰሙትም ያስተውሉታልና።
ከእንግዲህ ወዲያ ጣዖት ለኤፍሬም ምንድን ነው? እኔ አደከምሁት፤ አጸናሁትም፤ እኔ እንደ ተወደደ አበባ አፈራዋለሁ፤ ፍሬህም በእኔ ዘንድ ይገኛል።