አሕዛብ ለምን ዶለቱ? ወገኖችስ ለምን ከንቱ ይናገራሉ?
አሕዛብ ለምን በቍጣ ተነሣሡ? ሕዝቡስ ለምን በከንቱ አሤሩ?
አሕዛብ ለምን ያጉረመርማሉ? ለምንስ ከንቱዉን ያሰላስላሉ?
አሕዛብ ስለምን ያሤራሉ? ሕዝቦችስ ለምን በከንቱ ያድማሉ?
ልጨነቅ ቀርቤአለሁና፥ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።
ዘምሩ፥ ለአምላካችን ዘምሩ፤ ዘምሩ፥ ለንጉሣችን ዘምሩ።
እግዚአብሔር ለምድር ሁሉ ንጉሥ ነውና፤ በማስተዋል ዘምሩ፤
እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይውጣችኋል።
ወፍ ለእርስዋ ቤትን አገኘች፥ ዋኖስም ጫጩቶችዋን የምታኖርበት ቤት አገኘች፤ የኀያላን አምላክ ንጉሤም አምላኬም ሆይ፥ እርሱ መሠዊያህ ነው።
አሕዛብ ሆይ፥ ዕወቁና ደንግጡ፤ እስከ ምድር ዳርቻም ስሙ፤ ኀያላን! ድል ሁኑ፤ ዳግመኛም ብትበረቱ እንደ ገና ድል ትሆናላችሁ።
ገበሬዎቹ ግን ልጁን ባዩ ጊዜ እርስ በርሳቸው ‘ወራሹ ይህ ነው፤ ኑ፤ እንግደለውና ርስቱን እናግኝ፤’ ተባባሉ።
ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ ይዘብቱበታልም፤ ይሰድቡታልም፤ ይተፉበታልም።
ደስ ብሏቸውም ሠላሳ ብር ሊሰጡት ተስማሙ።
ሕዝቡም ተነሡባቸው፤ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፍፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ።
ይህንም በሰሙ ጊዜ ተበሳጩ፤ ጥርሳቸውንም አፋጩ፤ ሊገድሉአቸውም ወደዱ።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉ የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ድል ይነሣሉ።”