በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም በፊቱ አለፉ።
እነርሱ ለንጥቂያ እንደሚጓጓ አንበሳ፣ በስውርም እንደሚያደባ ደቦል አንበሳ ናቸው።
እርሱ ንጥቂያን እንደሚናፍቅ አንበሳ ተሸጉጦም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ደቦል ነው።
እነርሱ እንደ ተራቡ አንበሶች ወይም እንደ ሸመቁ ደቦል አንበሶች ናቸው።
ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።
ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።
በመጠን ኑሩ፤ ንቁም፤ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤