ለዘለዓለም አቆማቸው፤ ትእዛዝን ሰጣቸው፥ አላለፉምም።
ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤ የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።
ለዘለዓለም ዓለም አቆማቸው፥ ትእዛዝን ሰጠ፥ አያልፉትምም።
ምንጊዜም በማይፈርስ ድንጋጌ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም መሥርቶአቸዋል።
የሰማይን ሥርዐት፥ ከሰማይ በታችስ የሚሆነውን ታውቃለህን?
ጌታ እግዚአብሔር ተበቃይ ነው፥ እግዚአብሔር በግልጥ ተበቃይ ነው።
ከኖኅ ዘመን ውኃ ጀምሮ ይህ ለእኔ ምስክር ነው፤ ቀድሞ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን እንዳልቈጣት እንደ ማልሁ፥
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ የቀንና የሌሊት ቃል ኪዳኔን የሰማይንና የምድርንም ሥርዐት ያላጸናሁ እንደ ሆነ፥