ነፍሳቸው ትወጣለች፥ ወደ መሬትም ይመለሳሉ፤ ያንጊዜ ምክራቸው ሁሉ ይጠፋል።
ሥራህን አንዱ ትውልድ ለሌላው ትውልድ ያስተጋባል፤ ብርቱ ሥራህን ያውጃል።
ትውልደ ትውልድ ሥራህን ያመሰግናሉ፥ ኃይልህንም ያወራሉ።
አንድ ትውልድ የአንተን ሥራ ለሚቀጥለው ትውልድ ያስተላልፋል፤ ድንቅ ሥራህንም ይገልጣል።
እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፥ ቃልንም ከልባቸው የሚያወጡ አይደሉምን?
ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን።
እኔ ዛሬ እንደማደርግ ሕያዋን ብቻ ያመሰግኑሃል፤ ከዛሬ ጀምሮ ጽድቅህን የሚናገሩ ልጆችን እወልዳለሁ።
እግዚአብሔር ሕዝቡን ወደ እኔ ሰብስባቸው፤ እነርሱ በምድር ላይ በሕይወት በሚኖሩበት ዘመን ሁሉ እኔን መፍራት ይማሩና ለልጆቻቸውም ያስተምሩ ዘንድ ቃሌን ይስሙ ብሎኛልና በኮሬብ በተሰበሰባችሁ ጊዜ በፈጣሪያችሁ በእግዚአብሔር ፊት እንደ ቆማችሁ ንገራቸው።
ለልጆችህም አስተምረው፤ በቤትህም ስትቀመጥ፥ በመንገድም ስትሄድ፥ ስትተኛም፥ ስትነሣም አስተምረው።