መዝሙር 135:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማልክትን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ቤት፣ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ አመስግኑት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ቤት ውስጥ፥ በአምላካችን ቤት አደባባይ የምትቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአምላካችን መቅደስ፥ በእግዚአብሔር ቤት አደባባይ የምትቆሙ ሁሉ አመስግኑት! |
እንደ ሕዝቡም ልጆች እንደ ወንድሞቻችሁ በየአባቶች ቤቶች አከፋፈል በመቅደሱ ቁሙ፤ እንዲሁም ለሌዋውያን በየአባቶቻቸው ቤት አከፋፈል ይሁን፤
ሌዋውያኑም ኢያሱና ቀድምኤል፥ እንዲህ አሉ፥ “ቆማችሁ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም አምላካችንን እግዚአብሔርን አመስግኑ። የከበረ ስሙንም አመስግኑ፤ በበረከትና በምስጋናም ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አድርጉት።”
ሰማንያ አራት ዓመትም መበለት ሆና ኖረች፤ በጾምና በጸሎትም እያገለገለች፥ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቤተ መቅደስ አትወጣም ነበር።