እግዚአብሔር ከጽዮን ይባርክህ፤ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢየሩሳሌምን መልካምነት ታያለህ።
ብፁዕ ነው፤ ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ ሰው፤ ከጠላቶቻቸው ጋራ በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።
ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ሰው የታደለ ነው፥ ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ እርሱ አያፍርም።
እንደነዚህ ፍላጻዎች የሆኑ ብዙ ልጆች ያሉት ሰው የታደለ ነው፤ ከጠላቶቹ ጋር በፍርድ አደባባይ በሚከራከርበት ጊዜ ከቶ አይሸነፍም።
ዮሴፍም የኤፍሬምን ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ አየ። የምናሴ ልጅ የማኪር ልጆችም በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ።
ሰባትም ወንዶች፥ ሦስትም ሴቶች ልጆች ነበሩት።
ልጆቻቸው ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ይቀጠቅጡአቸዋል፤ መከራም ያጸኑባቸዋል፥ የሚታደጋቸውም የለም።