ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ አገልጋዩም አሞናዊው ጦቢያ፥ ዓረባዊውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፤ ቀላል አድርገውንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድን ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን?” አሉ።
መዝሙር 123:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውኃ ባሰጠሙን ነበር ብዬ በተጠራጠርሁ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነፍሳችን የቅንጡዎች ስድብ፣ የትዕቢተኞችም ንቀት እጅግ በዝቶባታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የትምክሕተኞችን ሹፈትና የትዕቢተኞችን ንቀት ነፍሳችን እጅግ ጠገበች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በትዕቢተኞች ብዙ መዋረድ፥ በትምክሕተኞችም ብዙ መናቅ ደርሶብናል። |
ሖሮናዊውም ሰንባላጥ፥ አገልጋዩም አሞናዊው ጦቢያ፥ ዓረባዊውም ጌሳም በሰሙ ጊዜ በንቀት ሳቁብን፤ ቀላል አድርገውንም ወደ እኛ መጡና፥ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድን ነው? በውኑ በንጉሡ ላይ ትሸፍቱ ዘንድ ትወድዳላችሁን?” አሉ።
እርሱ በተወሰነው ዕድሜ በሌሎች እንዲወድቅ፥ ቤቱም በኃጥኣን እንዲፈርስ ተዘጋጅቶአል። ነገር ግን ማንም ክፉ ሆኖ ንጹሕ እንደሚሆን አይመን።
እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ደንግጡ፤ ሴቶች ሆይ፥ እዘኑ፤ ልብሳችሁንም አውልቁ፤ ዕራቁታችሁንም ሁኑ፤ ወገባችሁንም በማቅ ታጠቁ።
እናንተ ባለጸጎች ሴቶች ሆይ፥ ተነሡ፤ ድምፄንም ስሙ፤ እናንተ ተማምናችሁ የምትቀመጡ ሴቶች ልጆች ሆይ፥ ንግግሬን አድምጡ።
“ሞአብ ከልጅነቷ ጀምራ ዐረፈች፤ በክብርዋም ቅምጥል ነበረች፤ ወይንዋም ከዕቃ ወደ ዕቃ አልተገላበጠም፤ ወደ ምርኮም አልሄደችም፤ ስለዚህ ቃናው በእርስዋ ውስጥ ቀርቶአል፤ መዓዛዋም አልተለወጠም።
እስራኤል ለአንተ መሳቂያ አልሆነምን? ወይስ በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን? ስለ እርሱ በተናገርህ ጊዜ ራስህን ትነቀንቃለህ።
የአቴና ሰዎችና በዚያም የነበሩ እንግዶች ሁሉ አዲስ ነገርን ከመናገርና ከመስማት በቀር ሌላ ዐሳብ አልነበራቸውም።
ይህንም ስለ ራሱ ሲናገር ሀገረ ገዢው ፊስጦስ መለሰ፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ፥ “ጳውሎስ ሆይ፥ ልታብድ ነውን? ብዙ ትምህርት እኮ ልብን ይነሣል” አለው።