ትእዛዛትህን እጅግ ይጠብቁ ዘንድ አንተ አዘዝህ።
እግዚአብሔርን የሚፈሩ ሁሉ፣ “ምሕረቱ ለዘላለም ነው” ይበሉ።
ቸር እንደሆነ፥ ፍቅሩም ለዘለዓለም እንደሆነ ጌታን የሚፈሩ ሁሉ አሁን ይንገሩ።
የሚፈሩት ሁሉ “የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው” ይበሉ።
ባልንጀራውን በስውር የሚያማን እርሱን አሳደድሁ፤ በዐይኑ ትዕቢተኛ የሆነውና ልቡ የሚሳሳው ከእኔ ጋር አይተባበርም።
በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለእግዚአብሔር እሰጣለሁ፥
የዐመፃን መንገድ ከእኔ አርቅ፥ በሕግህም ይቅር በለኝ፤
ድምፅም “ባሪያዎቹ ሁሉ እርሱንም የምትፈሩት ታናናሾችና ታላላቆች ሆይ! አምላካችንን አመስግኑ፤” ሲል ከዙፋኑ ወጣ።