መዝሙር 115:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ እኔ ባሪያህ ነኝ፥ ባሪያህ ነኝ፥ የሴት ባሪያህም ልጅ ነኝ፤ ሰንሰለቴን ሰበርህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤ እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤ በጕሮሯቸውም ድምፅ አይፈጥሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እጅ አላቸው አይዳስሱምም፥ እግር አላቸው አይሄዱምም፥ በጉሮሮአቸውም ድምፅ አያሰሙም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እጅ አላቸው፤ አይዳስሱም፤ እግር አላቸው፤ አይሄዱም፤ ድምፅም ማሰማት አይችሉም። |
ወርቁንና ብሩን ከኮሮጆ የሚያወጡና በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፤ እርሱም ጣዖት አድርጎ ይሠራዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል፤ ይሰግዱለትማል።
ቀድሞም እናንተ አሕዛብ በነበራችሁ ጊዜ ዲዳዎች ጣዖታትን ታመልኩ እንደ ነበር፥ ጣዖትም በማምለክ ረክሳችሁ እንደ ነበር፥ ወደ ወሰዱአችሁም ትሄዱ እንደ ነበር ታውቃላችሁ።
በነጋውም የአዛጦን ሰዎች ማለዱ፤ ወደ ዳጎንም ቤት ገቡ፤ እነሆም፥ ዳጎን በእግዚአብሔር ታቦት ፊት በምድር ላይ በግንባሩ ወድቆ አገኙት፤ ዳጎንንም አንሥተው በስፍራው አቆሙት።