ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ እግዚአብሔር ረዳትሽ ነውና፤
ምድር ሆይ፤ በጌታ ፊት፣ በያዕቆብ አምላክ ፊት ተንቀጥቀጪ፤
በያዕቆብ አምላክ ፊት፥ በጌታ ፊት ምድር ተናወጠች፥
ምድር ሆይ! በእግዚአብሔር ፊት፥ በያዕቆብም አምላክ ፊት በፍርሃት ተንቀጥቀጪ።
የሰማይ አዕማድ ይንቀጠቀጣሉ፥ ከተግሣጹም የተነሣ ይደነግጣሉ።
ምድርን ከሰማይ በታች ከመሠረቷ ያናውጣታል፥ ምሰሶዎችዋም ይንቀጠቀጣሉ።
ዝናባቸውን በረዶ አደረገው፥ እሳትም በምድራቸው ነደደ።
ለነፍሳቸው መብልን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት።
አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ብቻህን ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።
በውኑ እኔን አትፈሩምን? ከፊቴስ አትደነግጡምን? ይላል እግዚአብሔር፤ እንዳያልፍ አሸዋን በዘለዓለም ትእዛዝ ለባሕር ዳርቻ አድርጌአለሁ፤ ሞገዱም ቢትረፈረፍና ቢጮኽ ከእርሱ አያልፍም።