ከክፉ ነገርም አይፈራም፤ በእግዚአብሔር ለመታመን ልቡ የጸና ነው።
የእጁ ሥራ እውነተኛና ቅን ነው፤ ሥርዐቱም ሁሉ የታመነ ነው፤
የእጆቹ ሥራ እውነትና ፍርድ ናቸው፥ ትእዛዛቱም በሙሉ የታመኑ ናቸው፥
የሚያደርገው ሁሉ እውነትና ትክክል ነው፤ ትእዛዞቹም የታመኑ ናቸው።
ኀይሉን ያሳያቸው ዘንድ ስለ ስሙ አዳናቸው።
እነዚያ በፈረሶችና በሰረገላዎች ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።
እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።
አቤቱ፥ ድንቅን የምታደርግ አንተ ታላቅ ነህና፥ አንተም ብቻህን ታላቅ አምላክ ነህና፥
በማለዳ ምሕረትህን እንጠግባለንና፤ በዘመናችን ሁሉ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን።
አቤቱ፥ ሕዝብህን አዋረዱ፥ ርስትህንም አሠቃዩ።
ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመሰግናል፥ ግሩምና ቅዱስ ነውና።
እግዚአብሔር በሥራው እውነተኛ ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፤ እግዚአብሔር የታመነ ነው፤ ክፋትም የለበትም፤ እግዚአብሔር ጻድቅና ቸር ነው።
ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።”