ክብርና ባለጠግነት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
ሥራው ባለክብርና ባለግርማ ነው፤ ጽድቁም ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል።
ሥራው ምስጋናና ግርማ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።
የእግዚአብሔር ሥራ በክብርና በግርማ የተሞላ ነው፤ ጽድቁም ዘለዓለማዊ ነው።
በዚያም ዎፎች ይዋለዳሉ፥ የሸመላ ቤትም ይጐራበታቸዋል።
ከፀሐይ መውጫ ጀምሮ እስከ መግቢያው ድረስ የእግዚአብሔር ስሙ ይመስገን።
መካኒቱን በቤቱ የሚያኖራት፥ ደስ የተሰኘችም የልጆች እናት የሚያደርጋት።
በመከራህ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስምም ይቁምልህ።
አቤቱ፦ በአማልክት መካከል አንተን የሚመስል ማን ነው? በቅዱሳንም ዘንድ እንደ አንተ የከበረ ማን ነው? በምስጋና የተደነቅህ ነህ፤ ድንቅንም የምታደርግ ነህ፤
እንደ ልብስ ፈጥነው ያረጃሉና አይቈዩም፤ ብል እንደ በላውም ይሆናሉ፤ ጽድቄ ግን ለዘለዓለም፥ ማዳኔም ለልጅ ልጅ ይሆናል።
ብዙ ልዩ ልዩ የሆነች የእግዚአብሔር ጥበብ አሁን በቤተ ክርስቲያን በኩል በሰማያዊ ስፍራ ውስጥ ላሉት አለቆችና ሥልጣናት ትታወቅ ዘንድ፤