እግዚአብሔርን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
ሃሌ ሉያ። በቅኖች ሸንጎ፣ በጉባኤም መካከል፣ ለእግዚአብሔር በፍጹም ልቤ ምስጋና አቀርባለሁ።
ሃሌ ሉያ! በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም ጌታን በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ።
እግዚአብሔር ይመስገን! በቅኖች ሸንጎና በጉባኤም መካከል እግዚአብሔርን በሙሉ ልቤ አመሰግናለሁ።
ነፍሴ እግዚአብሔርን ታመሰግነዋለች፤ አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፤ መታመንንና የጌትነትን ክብር ለበስህ።
እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና።
በጥል ከበቡኝ፥ በከንቱም ተዋጉኝ።
አቤቱ፥ ፈተንኸኝ፥ ዐወቅኸኝም።
እግዚአብሔርን አዲስ ምስጋናን አመስግኑት፤ ምስጋናውም በጻድቃኑ ጉባኤ ነው።
ዘመኖች በፊትህ የተናቁ ናቸው፥ በማለዳም እንደ ሣር ያልፋል።
እኛ በቍጣህ አልቀናልና፥ በመቅሠፍትህም ደንግጠናልና።
አቤቱ፥ በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ፥ ታምራትህንም ሁሉ እናገራለሁ።