ውኃ በሌለበት ምድረ በዳ ተቅበዘበዙ፤ የሚኖሩበትንም ከተማ መንገድ አላገኙም።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ለሕዝብህ ሞገስ ስታድል ዐስበኝ፤ በምታድናቸውም ጊዜ ርዳኝ፤
አቤቱ፥ በሕዝብህ ሞገስ አስበኝ፥ በመድኃኒትህም ጐብኘኝ፥
እግዚአብሔር ሆይ! ሕዝብህን በምትረዳበት ጊዜ እኔንም አስታውሰኝ፤ እነርሱን በምታድንበት ጊዜ እኔንም አስበኝ።
አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ አስበኝ፤ ለእግዚአብሔርም ቤት ያደረግሁትን ወረታዬን አታጥፋ።
ሌዋውያኑንም ራሳቸውን እንዲያነጹ፥ መጥተውም በሮቹን እንዲጠብቁ፥ የሰንበትንም ቀን እንዲቀድሱ ነገርኋቸው። “አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ደግሞ አስበኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ራራልኝ” አልሁ።
በየጊዜውም ዕንጨት ለሚሸከሙ ሰዎች ቍርባን፥ ለበኵራቱም ሥርዐት አደረግሁ። “አምላካችን ሆይ፥ በመልካም አስበኝ።”
አምላኬ ሆይ፥ ለዚህ ሕዝብ ያደረግሁትን ሁሉ ለበጎነት አስብልኝ።
የምስጋናህን ቃል እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
ጌታችን ኢየሱስንም፥ “አቤቱ፥ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ ዐስበኝ” አለው።
ስምዖንም፥ እግዚአብሔር አስቀድሞ አሕዛብን ይቅር እንዳላቸውና ከውስጣቸውም ለስሙ ሕዝብን እንደ መረጠ ተናግሮአል።