ወንዞችን ምድረ በዳ አደረገ፥ የውኃውንም ምንጮች ደረቅ አደረጋቸው፤
የእግዚአብሔርንም መንፈስ ስላስመረሩት፣ ሙሴ የማይገባ ቃል ከአንደበቱ አወጣ።
እጅግ አስመርረውት ስለ ነበር ሙሴ ራሱን ባለመቈጣጠር ተናገረ።
ራሔልም ለያዕቆብ ልጅ እንዳልወለደች በአየች ጊዜ በእኅቷ ላይ ቀናችባት፤ ያዕቆብንም “ልጅ ስጠኝ፤ ይህስ ከአልሆነ እሞታለሁ” አለችው።
እርሱ ግን፦ ወደ እርስዋ ተመለከተና እንዲህ አላት፥ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፤ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉውን ነገርስ አንታገሥምን?” በዚህ በደረሰበት ሁሉ ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት በከንፈሩ አልበደለም።
“ከእኔ ምክርን የሚሸሽግ፥ በልቡም ነገርን የሚደብቅ ማን ነው? ከእኔ ይሰውረዋልን?
አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላካችን ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።
ሰውነቴ በላዬ ላይ ባለቀች ጊዜ አቤቱ፥ መንገዴን አንተ ታውቃለህ፤ በምሄድባት በዚያች መንገድ ወጥመድን ሰወሩብኝ።
እግዚአብሔርን በትዕግሥት ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ተመልሶ ሰማኝ፥ የልመናዬንም ቃል ሰማኝ።
ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።