ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከመስዕና ከባሕር፥ ከየሀገሩ ሰበሰባቸው።
ብፁዓን ናቸው፤ ፍትሕ እንዳይዛነፍ የሚጠብቁ፣ ጽድቅን ሁልጊዜ የሚያደርጉ፤
ፍርድን የሚጠብቁ፥ ጽድቅንም ሁልጊዜ የሚያደርጉ ብፁዓን ናቸው።
ፍትሕን የሚከተሉና ዘወትር ትክክለኛ የሆነውን ነገር የሚያደርጉ፥ እንዴት የተባረኩ ናቸው?
እግዚአብሔርን አልሁት፥ “አንተ ጌታዬ ነህ፤ በጎነቴን አትሻትምና።
የምስጋናህን ቃል እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
በቸርነትህ የሚታገሡ መንገድህንም የሚያስቡ ይገናኙሃል፤ እነሆ፥ አንተ ተቈጣህ፤ እኛም ኀጢአት ሠራን፤ ስለዚህም ተሳሳትን።
የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ሁሉ፥ እርሱ ወንድሜ ነው፤ እኅቴም፤ እናቴም፤” አለ።
እርሱም፥ “ብፁዓንስ የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተው የሚጠብቁ ናቸው” አላት።
የእንስላልና የጤና አዳም፥ ከአትክልትም ሁሉ ዐስራት የምታገቡ ፍርድንና የእግዚአብሔርን ፍቅር ቸል የምትሉ እናንተ ጻፎችና ፈሪሳውያን፥ ወዮላችሁ! ይህንም ልታደርጉ ይገባችኋል፥ ያንም አትተዉ።
ይህንም ዐውቃችሁ ብትሠሩ ብፁዓን ናችሁ።
እናንተስ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ካደረጋችሁ ወዳጆች ናችሁ።
እንዲሁ እኔም በእግዚአብሔርና በሰው ፊት ሁልጊዜ የማታወላውል ሕሊና ትኖረኝ ዘንድ እጋደላለሁ።
በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
በጎ ሥራ መሥራትን ቸል አንበል፥ በጊዜው እናገኘዋለንና።
“አምላክህን እግዚአብሔርን ውደድ፤ ሕጉንም፥ ሥርዐቱንም፥ ትእዛዙንም፥ ፍርዱንም በዘመንህ ሁሉ ጠብቅ።
“አትስረቅ።
ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።
ስለዚህ በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አሉ፤ ሌሊትና ቀንም በመቅደሱ ያመልኩታል፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው በእነርሱ ላይ ያድርባቸዋል።