ተናገረ፥ ዐውሎ ነፋስም ተነሣ፥ ሞገድም ከፍ ከፍ አለ።
በድንኳኖቻቸው ውስጥ አጕረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ድምፅ አላዳመጡም።
በድንኳኖቻቸውም ውስጥ አንጐራጐሩ፥ የጌታን ቃል አልሰሙም።
በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው አጒረመረሙ፤ የእግዚአብሔርንም ቃል አንሰማም አሉ።
የእስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ በሙሴና በአሮን ላይ አንጐራጐሩ።
በግብፅ ምድርና በምድረ በዳ ያደረግሁትን ተአምራቴንና ክብሬን ያዩ እነዚህ ሰዎች ሁሉ ዐሥር ጊዜ ስለ ተፈታተኑኝ፥ ቃሌንም ስላልሰሙ፥
“ዛሬ ቃሉን ብትሰሙ እነዚያ እንደ አሳዘኑት ጊዜ ልባችሁን አታጽኑ” ብሎአልና።