ቃሉን ልኮ ፈወሳቸው፥ ከጥፋታቸውም አዳናቸው።
ክብራቸው የሆነውንም ሣር በሚበላ፣ በበሬ ምስል ለወጡ።
ሣርም በሚበላ በበሬ ምሳሌ ክብራቸውን ለወጡ።
የእግዚአብሔርንም ክብር ሣር በሚበላ እንስሳ ምስል ለወጡ።
የአምላካችን የእግዚአብሔር ብርሃን በላያችን ይሁን። የእጆቻችንንም ሥራ ያቃናልናል።
ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረጸው፤ ቀልጦ የተሠራ ጥጃም አደረገው፤ እርሱም፥ “እስራኤል ሆይ፥ እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው” አላቸው።
አሕዛብ አማልክት ያልሆኑ አማልክቶቻቸውን ይለውጡ አንደ ሆነ እዩ፤ ነገር ግን ሕዝቤ ክብራቸውን ለማይረባ ነገር ለወጡ።