የእግዚአብሔርን ምሕረት ለሰው ልጆችም ያደረገውን ድንቁን ንገሩ፤
እርሱም የለመኑትን ሰጣቸው፤ ዳሩ ግን የሚያኰሰምን ሕመም ሰደደባቸው።
የለመኑትንም ሰጣቸው፥ ለነፍሳቸው ግን ክሳትን ላከ።
እርሱ የለመኑትን ሁሉ ሰጣቸው፤ ነገር ግን የሚያመነምን በሽታ አመጣባቸው።
ስለዚህም የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በክብርህ ላይ ውርደትን፥ በጌጥህ ላይም የሚነድና የሚያቃጥል እሳትን ይሰድዳል።
የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፥ የጻድቁን ድንቅ ተስፋ ከምድር ዳርቻ ሰምተናል። እነርሱ ግን፥ “የእግዚአብሔርን ሕግ ለሚያፈርሱ ወንጀለኞች ወዮላቸው!” አሉ።