እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርም አመኑ፤ ባሪያውንም ሙሴን አከበሩ።
መዝሙር 106:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልባቸው በመከራ ደከመ፤ ታመሙ የሚረዳቸውንም አጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ የተስፋ ቃሉን አመኑ፤ በዝማሬም አመሰገኑት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያን ጊዜ በቃሉ አመኑ፥ ምስጋናውንም ዘመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ በተስፋ ቃሉ አመኑ፤ የምስጋናም መዝሙር ዘመሩለት። |
እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፤ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፤ በእግዚአብሔርም አመኑ፤ ባሪያውንም ሙሴን አከበሩ።
በዚያ ጊዜም ሙሴና የእስራኤል ልጆች ይህን መዝሙር ለእግዚአብሔር ዘመሩ፤ እንዲህም ብለው ተናገሩ፦ “ለእግዚአብሔር እንዘምራለን፤ በክብር እጅግ ከፍ ከፍ ብሎአልና፤ ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር ጣለ።
በጭንጫም ላይ የወደቀው ሰምተው ነገሩን በደስታ የሚቀበሉት ናቸው፤ ነገር ግን ለጊዜው ያምናሉ እንጂ ሥር የላቸውም፤ መከራም በአገኛቸው ጊዜ ይክዳሉ።