ያስተምራቸውም ዘንድ መልካሙን መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናህንም ከአፋቸው አልከለከልህም፤ ለጥማታቸውም ውኃን ሰጠሃቸው።
መዝሙር 105:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም በሕዝቡ ላይ ቍጣን ተቈጣ፥ ርስቱንም ተጸየፈ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለመኑትም ጊዜ፣ ድርጭት አመጣላቸው፤ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለመኑ፥ ድርጭትንም አመጣላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ አጠገባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምግብ በጠየቁት ጊዜ ድርጭቶችን ላከላቸው። ከሰማይ እንጀራን ልኮ አጠገባቸው። |
ያስተምራቸውም ዘንድ መልካሙን መንፈስህን ሰጠሃቸው፤ መናህንም ከአፋቸው አልከለከልህም፤ ለጥማታቸውም ውኃን ሰጠሃቸው።
ሰውም ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ነገር ሁሉ በሕይወት እንዲኖር እንጂ ሰው በእንጀራ ብቻ በሕይወት እንዳይኖር ያስታውቅህ ዘንድ አስጨነቀህ፥ አስራበህም፤ አንተም ያላወቅኸውን፥ አባቶችህም ያላወቁትን መና መገበህ።
በነጋውም ከምድሪቱ ፍሬ ከበሉ በኋላ መናው ቀረ፤ ከዚያም በኋላ የእስራኤል ልጆች ዳግመኛ መና አላገኙም፤ በዚያው ዓመት የፊኒቆንን ምድር ፍሬ ሰበሰቡ።