በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ።
የተናገረው ቃል እስኪፈጸምለት፣ የእግዚአብሔር ቃል ፈተነው።
ቃሉ እስኪመጣለት ድረስ፥ የጌታ ቃል ፈተነው።
ዮሴፍ ራሱ አስቀድሞ የተናገረው እስኪፈጸም ድረስና የእግዚአብሔር ቃል ትክክለኛነቱን እስኪያረጋግጥለት ድረስ ነው።
ዮሴፍም ፈርዖንን አለው፥ “የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን አሳይቶታል።
የዚያን ጊዜ የጠጅ አሳላፊዎቹ አለቃ እንዲህ ብሎ ለፈርዖን ተናገረ፥ “እኔ ኀጢአቴን ዛሬ አስባለሁ፤
ስለ ቅንነትና ስለ የዋህነት ስለ ጽድቅም አቅና፥ ተከናወን፥ ንገሥም፤ ቀኝህም በክብር ይመራሃል።
የንጉሥ ልብ እንደ ውኃ ፈሳሽ በእግዚአብሔር እጅ ነው፤ ወደ ወደደውም ይመልሳታል፥ በዚያም ትቈያለች።
ከመከራውም ሁሉ አዳነው፤ በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊትም ሞገስንና ጥበብን ሰጠው፤ በግብፅና በቤቱ ሁሉ ላይ ቢትወደድ አድርጎ ሾመው።