ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በሁለቱ መካከል ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ንውጽውጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።
መዝሙር 104:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን የሚፈልግ ልብ ደስ ይበለው፤ እግዚአብሔርን ፈልጉት፥ ትጸናላችሁም፤ ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መላእክትህን መንፈስ፣ አገልጋዮችህንም የእሳት ነበልባል ታደርጋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነፋሳትን መልእክተኞቹ የሚያደርግ፥ የእሳት ነበልባልም አገልጋዮቹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነፋስ መልእክተኛህ ነው፤ የእሳት ነበልባልም አገልጋይህ ነው። |
ሁለቱም እየተነጋገሩ ሲሄዱ፥ እነሆ፥ የእሳት ሰረገላና የእሳት ፈረሶች በሁለቱ መካከል ገብተው ከፈሉአቸው፤ ኤልያስም በዐውሎ ነፋስ ንውጽውጽታ ወደ ሰማይ ወጣ።
ኤልሳዕም፥ “አቤቱ፥ ያይ ዘንድ ዐይኖቹን፥ እባክህ፥ ግለጥ” ብሎ ጸለየ። እግዚአብሔርም የብላቴናውን ዐይኖች ገለጠ፤ እነሆም፥ የእሳት ፈረሶችና ሰረገሎች በኤልሳዕ ዙሪያ ተራራውን ሞልተውት አየ።
በእንስሶቹም መካከል እንደሚነድድ የእሳት ፍም ያለ አምሳያ ነበረ፤ በእንስሶቹ መካከል ወዲህና ወዲያ የሚሄድ እንደ ፋና ያለ አምሳያ ነበረ፤ ለእሳቱም ፀዳል ነበረው፤ ከእሳቱም መብረቅ ይወጣ ነበር።
ሰዱቃውያን፥ “ሙታን አይነሡም፤ መልአክም የለም፤ መንፈስም የለም” ይላሉና፤ ፈሪሳውያን ግን ይህ ሁሉ እንዳለ ያምናሉ።
መላእክት ሁሉ መናፍስት አይደሉምን? የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ ስለ አላቸው ሰዎችስ ለአገልግሎት ይላኩ የለምን?