ባሪያውን ሙሴን፥ የመረጠውንም አሮንን ላከ።
መርከቦች በላይዋ ይመላለሳሉ፤ አንተ የፈጠርኸውም ሌዋታን በውስጧ ይፈነጫል።
በዚያ ላይ መርከቦች ይሄዳሉ፥ በዚያም ላይ የፈጠርኸው ዘንዶ ያጫውትሃል።
በላዩ መርከቦች ይመላለሳሉ፤ በውስጡም አንተ የፈጠርከው ሌዋታን የተባለ ታላቅ ዘንዶ ይጫወታል።
“ዛብሎን ጫማውን አዝቦ ይኖራል፤ እርሱም እንደ መርከቦች ወደብ ይሆናል፤ ዳርቻውም እስከ ሲዶና ይሰፋል።
ውኃውም አሸነፈ፤ በምድር ላይም እጅግ በዛ፤ መርከቢቱም በውኃ ላይ ተንሳፈፈች።
ነገር ግን ሌዋታንን ለመግደል የተዘጋጀ ያችን ቀን የሚረግም ይርገማት።
በዚያም ቀን እግዚአብሔር በፈጣኑ እባብ ደራጎን ላይ፥ በክፉውም እባብ ደራጎን ላይ ልዩ፥ ታላቅና ብርቱ ሰይፍን ያመጣል። በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድለዋል።
በአንቺ ውስጥ የነበሩ የጌባል ሽማግሌዎችና ጥበበኞችዋ ስብራትሽን ይጠግኑ ነበር፤ ከአንቺም ጋር ይነግዱ ዘንድ የባሕር መርከቦች ሁሉና መርከበኞቻቸው በመካከልሽ ነበሩ።