በምድር ላይ ራብን አመጣ፥ የእህልን ኀይል ሁሉ አጠፋ።
ደግሞም የእግዚአብሔር ዛፎች፣ እርሱ የተከላቸውም የሊባኖስ ዝግባዎች ጠጥተው ይረካሉ፤
የጌታ ዛፎች እርሱም የተከላቸው የሊባኖስ ዝግባዎች ይጠግባሉ።
እግዚአብሔር የተከላቸው የሊባኖስ ዛፎች በቂ ዝናብ ያገኛሉ፤
መቅሠፍቱ ከቍጣው ነውና፥ መዳንም ከፈቃዱ ነውና፤ ማታ ልቅሶ ይሰማል፥ ጥዋት ግን ደስታ ይሆናል።
አቤቱ፥ ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የተዘጋጀ ነው፥ አንተም መቼም መች እስከ ዘለዓለም ነህ።
ከፍ ባለው በእስራኤል ተራራ ላይ እተክለዋለሁ፤ ቅርንጫፎችንም ያወጣል፤ ፍሬም ያፈራል፤ ታላቅም ዝግባ ይሆናል፤ በበታቹም ወፎች ሁሉ ያርፋሉ፤ በቅርንጫፎቹም ጥላ በክንፍ የሚበርር ሁሉ ይጠጋል፤ ቅርንጫፉም ይሰፋል።
እንደሚጋርዱ ዛፎች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ የተክል ቦታዎች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከላቸው ድንኳኖች በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ናቸው።