Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 104:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 የቀ​ባ​ኋ​ቸ​ውን አት​ዳ​ስሱ፥ በነ​ቢ​ያ​ቴም ላይ ክፉ አታ​ድ​ርጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 የሰውን ልብ ደስ የሚያሰኝ ወይን፣ ፊቱን የሚያወዛ ዘይት፣ ልቡን የሚያበረታ እህል በዚህ ይገኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ወይን የሰውን ልብ ደስ ያሰኛል፥ ዘይትም ፊትን ያበራል፥ እህልም የሰውን ጉልበት ያጠነክራል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ ልቡን ደስ የሚያሰኝ የወይን ጠጅ፥ ፊቱን የሚያበራ ዘይትና ብርታት የሚሰጠውን ምግብ ያዘጋጃል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 104:15
30 Referencias Cruzadas  

እርሱ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ በረ​ከ​ትን ይቀ​በ​ላል፥ ምሕ​ረ​ቱም ከአ​ም​ላኩ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ነው።


ሰነ​ፎች ሰዎች እን​ጀ​ራን ለሣቅ ያደ​ር​ጉ​ታል፥ የወ​ይን ጠጅም ሕያ​ዋ​ንን ደስ ያሰ​ኛል፥ ሁሉም ለገ​ን​ዘብ ይገ​ዛል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሥራ​ህን ተቀ​ብ​ሎ​ታ​ልና፦ ና እን​ጀ​ራ​ህን በደ​ስታ ብላ፥ በበጎ ልቡ​ናም የወ​ይን ጠጅ​ህን ጠጣ።


ወይ​ኑም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንና ሰውን ደስ የሚ​ያ​ሰ​ኘ​ውን የወ​ይን ጠጅ​ነ​ቴን ትቼ በዛ​ፎች ላይ እነ​ግሥ ዘንድ ልሂ​ድን? አላ​ቸው።


“ጽድ​ቅን ወደ​ድህ፤ ዐመ​ፃ​ንም ጠላህ፤ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክህ እን​ዳ​ንተ ካሉት ይልቅ የሚ​በ​ልጥ የደ​ስታ ዘይ​ትን ቀባህ።”


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።


እናንተም ከቅዱሱ ቅባት ተቀብላችኋል፥ ሁሉንም ታውቃላችሁ።


ደግ​ሞም እን​ዲህ አለኝ፥ “የሰው ልጅ ሆይ! የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን እን​ጀራ በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ፤ በች​ግር እያሉ እን​ጀ​ራን በሚ​ዛን ይበ​ላሉ፥ እየ​ደ​ነ​ገ​ጡም ውኃን በልክ ይጠ​ጣሉ፤


ይመ​ጣሉ፤ በጽ​ዮ​ንም ተራራ ደስ ይላ​ቸ​ዋል፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በጎ​ነት፥ ወደ እህ​ልና ወደ ወይን ጠጅ፥ ወደ ዘይ​ትም፥ ወደ በጎ​ችና ወደ ላሞች ሀገ​ርም ይሰ​በ​ሰ​ባሉ፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም እንደ ረካች ገነት ትሆ​ና​ለች፤ ከእ​ን​ግ​ዲ​ህም ወዲህ አይ​ራ​ቡም።


ወይ​ራዋ ግን፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዎ​ችን የሚ​ያ​ከ​ብ​ር​በ​ትን ቅባ​ቴን ትቼ በዛ​ፎች ላይ ለመ​ን​ገሥ ልሂ​ድን? አለ​ቻ​ቸው።


አንተ ራሴን እንኳ ዘይት አል​ቀ​ባ​ኸ​ኝም፤ እር​ስዋ ግን እግ​ሬን ሽቱ ቀባ​ችኝ።


እነሆ፥ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና ከይ​ሁዳ ኀይ​ለ​ኛ​ውን ወን​ድና ኀይ​ለ​ኛ​ዋን ሴት፥ የእ​ን​ጃ​ራን ኀይል ሁሉ፥ የው​ኃ​ው​ንም ኀይል ሁሉ ያስ​ወ​ግ​ዳል፤


ዐዋ​ቂ​ዎ​ችን ማን ያው​ቃ​ቸ​ዋል? ቃላ​ቸ​ው​ንስ መተ​ር​ጐም የሚ​ያ​ውቅ ማን ነው? የሰው ጥበቡ ፊቱን ታበ​ራ​ለች፥ በፊ​ቱም ኀፍ​ረት የሌ​ለው ሰው ይጠ​ላል።


ሙሴ​ንም፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ደ​ሰ​ውን አሮ​ን​ንም በሰ​ፈር አስ​ቈ​ጧ​ቸው።


የወ​ይራ ዛፍ በሀ​ገ​ርህ ሁሉ ይሆ​ን​ል​ሃል፤ ፍሬ​ውም ይረ​ግ​ፋ​ልና ዘይ​ቱን አት​ቀ​ባም።


ሰውም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አፍ በሚ​ወጣ ነገር ሁሉ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ኖር እንጂ ሰው በእ​ን​ጀራ ብቻ በሕ​ይ​ወት እን​ዳ​ይ​ኖር ያስ​ታ​ው​ቅህ ዘንድ አስ​ጨ​ነ​ቀህ፥ አስ​ራ​በ​ህም፤ አን​ተም ያላ​ወ​ቅ​ኸ​ውን፥ አባ​ቶ​ች​ህም ያላ​ወ​ቁ​ትን መና መገ​በህ።


በእ​ህል ረሃብ ባስ​ጨ​ነ​ክ​ኋ​ችሁ ጊዜ ዐሥር ሴቶች እን​ጀራ በአ​ንድ ምጣድ ይጋ​ግ​ራሉ፤ በሚ​ዛ​ንም መዝ​ነው እን​ጀ​ራ​ች​ሁን ይመ​ል​ሱ​ላ​ች​ኋል፤ በበ​ላ​ች​ሁም ጊዜ አት​ጠ​ግ​ቡም።


ጽዋንም አንሥቶ አመስግኖም ሰጣቸው፤ ሁሉም ከእርሱ ጠጡ።


“የሰው ልጅ ሆይ! ምድር ብት​በ​ድ​ለኝ፥ ብት​ስት፥ ኀጢ​አ​ትም ብት​ሠራ እጄን በእ​ር​ስዋ አነ​ሣ​ለሁ፤ የእ​ህ​ሉ​ንም ኀይል አጠ​ፋ​ለሁ፤ በእ​ር​ስ​ዋም ረሀ​ብን እል​ካ​ለሁ፤ ከብ​ቱ​ንና ሰዉ​ንም ከእ​ር​ስዋ አጠ​ፋ​ለሁ።


ለማ​ጥ​ፋ​ትም የሆ​ነ​ውን፥ አጠ​ፋ​ች​ሁም ዘንድ የም​ሰ​ድ​ደ​ውን የራብ ፍላጻ በላ​ያ​ችሁ በሰ​ደ​ድሁ ጊዜ፥ ራብን እጨ​ም​ር​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ የእ​ን​ጀ​ራ​ች​ሁ​ንም በትር እሰ​ብ​ራ​ለሁ።


ከዛ​ፉም ሥር ዕረፉ፤ እን​ጀ​ራም እና​ም​ጣ​ላ​ች​ሁና ብሉ፤ ከዚ​ያም በባ​ሪ​ያ​ችሁ ዘንድ ከአ​ረ​ፋ​ችሁ በኋላ፥ ወደ ዐሰ​ባ​ች​ሁት ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “እን​ዳ​ልህ እን​ዲሁ አድ​ርግ” አሉት።


በአ​ራ​ተ​ኛ​ውም ቀን ማል​ደው ተነሡ፤ እር​ሱም ለመ​ሄድ ተነሣ፤ የብ​ላ​ቴ​ና​ዪ​ቱም አባት አማ​ቹን፥ “ሰው​ነ​ት​ህን በቁ​ራሽ እን​ጀራ አበ​ርታ፤ ከዚ​ያም በኋላ ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ” አለው።


አቤ​ሴ​ሎ​ምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደ​ረገ፤ አቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮ​ቹን፥ “አም​ኖን የወ​ይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ፦ አም​ኖ​ንን ግደሉ ባል​ኋ​ችሁ ጊዜ ግደ​ሉት። አት​ፍ​ሩም፤ ያዘ​ዝ​ኋ​ች​ሁም እኔ ነኝና በርቱ፤ ጽኑም” ብሎ አዘ​ዛ​ቸው።


ብዙ ዝና​ምና በረዶ ከሰ​ማይ እን​ደ​ሚ​ወ​ርድ፥ ምድ​ርን እን​ደ​ሚ​ያ​ረ​ካት፥ ታበ​ቅ​ልና ታፈ​ራም ዘንድ እን​ደ​ሚ​ያ​ደ​ር​ጋት፥ ዘርን ለሚ​ዘራ፥ እህ​ል​ንም ለም​ግብ እን​ደ​ሚ​ሰጥ እንጂ ወደ ሰማይ እን​ደ​ማ​ይ​መ​ለስ፥


የኤፍሬምም ሰዎች እንደ ኃያላን ይሆናሉ፥ ልባቸውም የወይን ጠጅ እንደ ጠጣ ሰው ደስ ይለዋል፣ ልጆቻቸውም አይተው ደስ ይላቸዋል፥ ልባቸውም በእግዚአብሔር ሐሤት ያደርጋል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios