የዱር ዛፎች ሁሉ፥ የተከልኸው የሊባኖስ ዝግባም ይጠግባሉ።
ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ግን ድራሹ ይጠፋል፤ ምልክቱም በቦታው አይገኝም።
ነፋስ በነፈሰበት ጊዜ ያልፋልና፥ ስፍራውንም ደግሞ አያውቀውምና።
የዱር አበባ ነፋስ በሚነፍስበት ጊዜ ወዲያው ይጠፋል፤ በዚያ ስፍራ እንደ ነበረ እንኳ አይታወቅም።
ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ ስላሰኘው አልተገኘም፤ እግዚአብሔር ሰውሮታልና።
ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እንግዲህ አይኖርም።
ዐይን አየችው፤ ነገር ግን ዳግመኛ አታየውም፤ ስፍራውንም ከእንግዲህ ወዲህ አያውቀውም።
“ጩኽ” የሚል ሰው ቃል፤ “ምን ብዬ ልጩኽ?” አልሁ። “ሥጋ ለባሽ ሁሉ ሣር ነው፤ የሰውም ክብሩ ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነው።
የእግዚአብሔር እስትንፋስ ይነፍስበታልና ሣሩ ይደርቃል፤ አበባውም ይረግፋል፤ በእውነት ሕዝቡ ሣር ነው።