ሰማይ ከምድር ከፍ እንደሚል፥ እንዲሁ እግዚአብሔር ምሕረቱን በሚፈሩት ላይ አጸና።
ዘመኖቼ እንደ ምሽት ጥላ ናቸው፤ እኔም እንደ ሣር ደርቄአለሁ።
ከቁጣህና ከመዓትህም የተነሣ፥ አንሥተኸኛልና፥ ጥለኸኝማልና።
የሕይወቴ ዘመን እንደ ማታ ጥላ ሆኖአል፤ እንደ ሣርም እጠወልጋለሁ።
እንደ አበባ ይወጣል፥ ይረግፋልም፤ እንደ ጥላም ያልፋል፥ እርሱም አይኖርም።
በዚህና በዚያ አፈረሰኝ፤ እኔም ሄድሁ፤ ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ቈረጠው።
የልጅ ልጆች ሥራህን ያደንቃሉ፥ ኀይልህንም ይናገራሉ፥
ሰው በከንቱ ወራቱ ቍጥርና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማን ነው? ወይስ ለሰው ከፀሓይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?
አሌፍ። በቍጣው በትር ችግር ያየ ሰው እኔ ነኝ።
ሕይወታችሁ ምንድር ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፍዋለት ናችሁና።
“ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሣር አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤