ምሳሌ 8:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፥ የቀላያትን ምንጮች ባጸና ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደመናትን በላይ ባጸና ጊዜ፣ የውቅያኖስን ምንጮች በመሠረተ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደመናትን በላይ ባዘጋጀ ጊዜ፥ የቀላይን ምንጮች ባጸና ጊዜ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደመናትን በጠፈር ባኖረበት ጊዜ፥ የውቅያኖስን ምንጭ በከፈተ ጊዜ፥ |
እግዚአብሔርም ከሰማይ በታች ያለው ውኃ በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ። ከሰማይ በታች ያለው ውኃም በመጠራቀሚያው ተሰበሰበ፤ የብሱም ተገለጠ።
በኖኅ ዕድሜ በስድስተኛው መቶ ዓመት በሁለተኛው ወር ከወሩም በዐሥራ ሰባተኛው ዕለት፥ በዚያው ቀን የታላቁ ቀላይ ምንጮች ሁሉ ተነደሉ፤ የሰማይ መስኮቶችም ተከፈቱ፤