ምሳሌ 8:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሚወድዱኝ ሀብትን እከፍላቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም በመልካም ነገር እሞላ ዘንድ። የሚሆነውን ነገር በየቀኑ ብነግራችሁ ከጥንት ጀምሮ የነበረውን ቍጥር አስባለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለሚወድዱኝ ብልጽግና እሰጣለሁ፤ ግምጃ ቤታቸውንም እሞላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሚወድዱኝ ርስት አወርሳቸው ዘንድ ቤተ መዛግብታቸውንም እሞላ ዘንድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚወዱኝ ሀብትን እሰጣቸዋለሁ፤ ቤታቸውንም በብልጽግና እሞላዋለሁ። |
እና የእግዚአብሔር ልጆች ከሆን ወራሾቹ ነን፤ የእግዚአብሔር ወራሾች ከሆንም የክርስቶስ ወራሾቹ ነን፤ በመከራ ከመሰልነውም በክብር እንመስለዋለን።
በእስራቴም ጊዜ ከእኔ ጋር በመከራ ተባብራችኋል፤ የገንዘባችሁንም መዘረፍ በደስታ ተቀብላችኋል፤ በሰማያት ለዘለዓለም የሚኖር ከዚህ የሚበልጥና የተሻለ ገንዘብ እንዳላችሁ ታውቃላችሁና።
ችግረኛውን ከመሬት ያነሣዋል፤ ምስኪኑንም ከጕድፍ ያነሣዋል፤ ከሕዝቡ መኳንንት ጋር ያስቀምጠው ዘንድ፥ የክብርንም ዙፋን ያወርሰው ዘንድ።