ምሳሌ 8:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተስ ጥበብን አስተምር፥ ማስተዋል ትመልስልህ ዘንድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጥበብ ጮኻ አትጣራምን? ማስተዋልስ ድምፅዋን ከፍ አድርጋ አታሰማምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በውኑ ጥበብ አትጮኽምን? ማስተዋልስ ድምፅዋን አታሰማምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አድምጡ! ጥበብ ትጣራለች፤ ማስተዋልም ድምፅዋን ታሰማለች። |
በኋለኛዪቱ በታላቅዋ የበዓል ቀንም ጌታችን ኢየሱስ ቆመና ድምፁን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፥ “የተጠማ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ።
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኀይልን ትቀበላላችሁ፤ በኢየሩሳሌምና በይሁዳ ሁሉ፥ በሰማርያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረስም ምስክሮች ትሆኑኛላችሁ።”
ለእኛ ለዳንነው ግን ከአይሁድ፥ ከአረሚም ብንሆን ክርስቶስ የእግዚአብሔር ኀይል ነው፤ የእግዚአብሔርም ጥበብ ነው።