በቤቷም አቅራቢያ ባለው መንገድ ሲሄድ ሲናገርም፤
የቤቷን አቅጣጫ ይዞ፣ በቤቷ ማእዘን አጠገብ ባለው መንገድ ያልፍ ነበር፤
በአደባባይ ሲሄድ በቤትዋም አቅራቢያ ሲያልፍ፥ የቤትዋን መንገድ ይዞ ወደ እርሷ አቀና፥
አንዲት ሴት በምትኖርበት ቤት አጠገብ ባለው መንገድ ማእዘን ያልፍ ነበር፤ ወደ ቤትዋም አቅጣጫ ይራመድ ነበር፤
መንገድህን ከእርስዋ አርቅ፥ ወደ ቤቷም ደጅ አትቅረብ፥
አንድ ጊዜ በጎዳና፥ በሌላ ጊዜም በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።
ቤቷ ወደ ሞት ጓዳ የሚያወርድ የሲኦል መንገድ ነው።
ከዝሙት ራቁ፤ ኀጢአት የሚሠራ ሰው ሁሉ ከሥጋው ውጭ ይሠራልና፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን ራሱ በሥጋው ላይ ኀጢአትን ይሠራል።
ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፤ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።
አንዳንዶችንም በሥጋ የረከሰውን ልብስ እንኳ እየጠላችሁ በፍርሃት ማሩ።
ሶምሶንም ወደ ጋዛ ሄደ፥ በዚያም ጋለሞታ ሴት አይቶ ወደ እርስዋ ገባ።