በዚያም ብዙ ቀን ተቀመጠ። የፍልስጥኤም ንጉሥ አቤሜሌክም በመስኮት ሆኖ በተመለከተ ጊዜ ይስሐቅን ከሚስቱ ከርብቃ ጋር ሲጫወት አየው።
ምሳሌ 7:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቤትWa መስኮት ሆና ወደ ዐደባባይ ትመለከታለችና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቤቴ መስኮት፣ በዐይነ ርግቡ ወደ ውጭ ተመለከትሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤቴ መስኮት ሆኜ ወደ አደባባይ ተመለከትሁ፥ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዕለታት አንድ ቀን በቤቴ መስኮት ወደ ውጪ እመለከት ነበር፤ |
በዚያም ብዙ ቀን ተቀመጠ። የፍልስጥኤም ንጉሥ አቤሜሌክም በመስኮት ሆኖ በተመለከተ ጊዜ ይስሐቅን ከሚስቱ ከርብቃ ጋር ሲጫወት አየው።
የእግዚአብሔርም ታቦት ወደ ዳዊት ከተማ በደረሰች ጊዜ የሳኦል ልጅ ሜልኮል በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ ንጉሡም ዳዊት በእግዚአብሔር ፊት ሲዘልልና ሲዘምር አየችው፥ በልብዋም ናቀችው።
ልጅ ወንድሜ በቤቴል ተራሮች ላይ ሚዳቋን ወይም የዋሊያን እንምቦሳ ይመስላል፤ እነሆ፥ በመስኮቶች ሲጐበኝ፥ በዐይነ ርግብም ሲመለከት፥ እርሱ ከቅጥራችን በኋላ ቆሞአል።
የሲሣራ እናት በመስኮት ሆና ተመለከተች፤ በሰቅሰቅም ዘልቃ፦ ከሲሣራ የተመለሰ እንዳለ አየች፤ ስለምን ለመምጣት ሰረገላው ዘገየ? ስለምንስ የሰረገላው መንኰራኵር ቈየ? ብላ ጮኸች።