እነርሱም፥ “ወዲያ ሂድ፤ ከእኛ ጋር ልትኖር መጣህ እንጂ ልትገዛን አይደለም፤ አሁንም ከእነርሱ ይልቅ አንተን እናሠቃይሃለን” አሉት።
ምሳሌ 5:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ትላለህ፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ! ልቤም ከተግሣጽ እንዴት ራቀ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም ትላለህ፤ “ምነው ተግሣጽን ጠላሁ! ልቤስ ምነው መታረምን ናቀ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ትላለህም፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ፥ ልቤም ዘለፋን ናቀ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህም ትላለህ፦ “የማልማረውና የሰውን ተግሣጽ የማልቀበለው ከቶ ለምንድን ነው! |
እነርሱም፥ “ወዲያ ሂድ፤ ከእኛ ጋር ልትኖር መጣህ እንጂ ልትገዛን አይደለም፤ አሁንም ከእነርሱ ይልቅ አንተን እናሠቃይሃለን” አሉት።
እርሱም ይህን ሲናገር ንጉሡ አሜስያስ፥ “በውኑ የንጉሡ አማካሪ ልትሆን ሹሜሃለሁን? ቅጣት እንዳያገኝህ ተጠንቀቅ” አለው። ነቢዩም፥ “ይህን አድርገሃልና፥ ምክሬንም አልሰማህምና እግዚአብሔር ሊያጠፋህ እንዳሰበ አወቅሁ” ብሎ ዝም አለ።
እነርሱ ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በሕዝቡ ላይ እስኪወጣ ድረስ፥ ፈውስም እስከማይገኝላቸው ድረስ፥ በእግዚአብሔር መልእክተኞች ይሳለቁ፥ ቃሉንም ያቃልሉ፥ በነቢያቱም ላይ ያፌዙ ነበር።
“ይህን ያህል ዘመን የዋሃን ጽድቅን ሲከተሉ አያፍሩም። ሰነፎች፥ እስከ መቼ ድረስ ስሕተትን ትወዳላችሁ? ሰነፎች ስድብን የሚወዱ ናቸው፥ ሰነፎችም ሆነው ዕውቀትን ጠሉ። ለሚዘልፏቸው የተመቹ ሆኑ፤
የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ዕውቀት ለሚያደርጋት ሁሉ መልካም ናት። እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፥ ሰነፎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።
አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ዐዋቂ ነው። እውነት ከበዛ ዘንድ ብዙ ኀይል አለ፥ ኀጢአተኞች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፥