ባዕዳን በሀብትህ እንዳይጠግቡ፥ የድካምህም ፍሬ በባዕድ ሰው ቤት እንዳይገባ።
ባዕዳን በሀብትህ እንዳይፈነጥዙ፣ ልፋትህም የሌላውን ሰው ቤት እንዳያበለጽግ ነው።
ሌሎች ከኃይልህ እንዳይጠግቡ፥ ድካምህም ወደ ባዕድ ሰው ቤት እንዳይሄድ።
ሀብትህን ሁሉ ባዕዳን ሰዎች ይወስዱታል፤ የደከምክበትም ንብረት ለሌላ ሰው ይሆናል።
ሰውነትህ በደከመ ጊዜ፥ ኋላ ትጸጸታለህ፥
ሕይወትህን ለሌላ እንዳትሰጥ፥ ንብረትህንም ምሕረት ለሌላቸው፤
የአመንዝራ ሴት ክብር እስከ አንዲት እንጀራ ነው፤ አመንዝራ ሴትም የተከበሩ ወንዶች ነፍስን ታጠምዳለች።
የጠብ ካሣ በምንም አይለወጥም፥ በገንዘብ ብዛትም አይታረቀውም።
ጠላት ጕልበቱን በላው፤ እርሱ ግን አላወቀም፤ ሽበትም ወጣበት፤ እርሱም ገና አላስተዋለም።
ከአመንዝሮች ጋር ገንዘብህን ሁሉ የጨረሰ ይህ ልጅህ በተመለሰ ጊዜ ግን የሰባውን ፍሪዳ አረድህለት።’