ዳዊትም፥ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፤ ለእግዚአብሔርም የሚሠራው ቤት እጅግ ማለፊያና በሀገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እንዲጠራ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ስለዚህ አዘጋጅለታለሁ” አለ። ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ አዘጋጀ።
ምሳሌ 4:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔም አባቴን የምሰማ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ፊት እወደድ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአባቴ ቤት ገና ለግላጋ ወጣት፣ ለእናቴም አንድ ልጇ ብቻ በነበርሁ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም አባቴን የምሰማ ትንሽ ልጅ ነበርሁና፥ በእናቴም ዘንድ እወደድ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔም አንድ ጊዜ ከአባቴ ጋር የምኖር ትንሽ ልጅ ነበርኩ፤ ለእናቴም አንድ ነበርኩ፤ |
ዳዊትም፥ “ልጄ ሰሎሞን ታናሽና ለጋ ብላቴና ነው፤ ለእግዚአብሔርም የሚሠራው ቤት እጅግ ማለፊያና በሀገሩ ሁሉ ስሙና ክብሩ እንዲጠራ ይሆን ዘንድ ይገባል፤ ስለዚህ አዘጋጅለታለሁ” አለ። ዳዊትም ሳይሞት አስቀድሞ ብዙ አዘጋጀ።
ንጉሡ ዳዊትም ለጉባኤው ሁሉ እንዲህ አለ፥ “እግዚአብሔር ብቻውን የመረጠው ልጄ ሰሎሞን ገና ለጋ ብላቴና ነው፤ ሕንጻው ግን ለእግዚአብሔር ለአምላክ ነው እንጂ ለሰው አይደለምና ሥራው ታላቅ ነው።
በዳዊትም ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የሞገስንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ፣ ወደ እርሱም ወደ ወጉት ይመለከታሉ፣ ሰውም ለአንድያ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኵር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።
እርስ በርሳችሁም በአንድ ዐሳብ ተስማሙ፤ ትዕቢትን ግን አታስቡ፤ ራሱን የሚያዋርደውንም ሰው ምሰሉ፤ እና ዐዋቆች ነን አትበሉ።