“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
ምሳሌ 4:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካም ስጦታን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎ ትምህርት እሰጣችኋለሁ፤ ስለዚህ ትምህርቴን አትተዉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ትምህርትን እሰጣችኋለሁና፥ ሕጌን አትተዉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ የማስተምራችሁ ትምህርት መልካም ስለ ሆነ ቸል አትበሉት። |
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፥ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ይመረምራልና፥ የነፍስንም አሳብ ሁሉ ያውቃልና የአባቶችህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በነፍስህ ፈቃድም ተገዛለት፤ ብትፈልገው ታገኘዋለህ፤ ብትተወው ግን ለዘለዓለም ይተውሃል።
“እናንተ ግን ብትመለሱ፥ የሰጠኋችሁን ሥርዐቴንና ትእዛዜን ብትተዉ፥ ሄዳችሁም ሌሎችን አማልክት ብታመልኩ፥ ብትሰግዱላቸውም፥
እኛም የአባታችንን የሬካብ ልጅ የኢዮናዳብን ቃል ባዘዘን ነገር ሁሉ ታዝዘናል፤ እኛም ሚስቶቻችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችንም ዕድሜአችንን ሙሉ የወይን ጠጅ አልጠጣንም፤
ትምህርቴንም እንደ ዝናም ተስፋ ታድርገው፤ ነገሬ እንደ ጠል ይውረድ፤ በእርሻም ላይ እንደ ዝናም፥ በሣርም ላይ እንደ ጤዛ።