ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።
ምሳሌ 4:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በክፉዎች መንገድ አትሂድ፥ በክፉ ሰዎችም ጎዳና አትቅና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ኃጥኣን ጐዳና እግርህን አታንሣ፤ በክፉ ሰዎች መንገድ አትሂድ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በክፉዎች መንገድ አትግባ፥ በመጥፎ ሰዎችም ጎዳና አትሂድ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰዎች በሚሄዱበት መንገድ አትሂድ፤ ምሳሌነታቸውንም አትከተል። |
ምስጉን ነው፥ በዝንጉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኀጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ ሰው።