በመንገድህም ሁሉ በመተማመን ትሄዳለህ፥ እግሮችህም አይሰነካከሉም።
ከዚያም መንገድህን ያለ ሥጋት ትሄዳለህ፤ እግርህም አይሰናከልም፤
የዚያን ጊዜ መንገድህን ተማምነህ ትሄዳለህ፥ እግርህም አይሰነካከልም።
በመንገድህ ያለ ፍርሀት ተማምነህ መሄድ ትችላለህ፤ ከቶም አትሰናከልም።
ኢየሩሳሌምስ እንደ ከተማ የታነጸች ናት።
ስለ ወንድሞቼና ስለ ባልንጀሮቼ ስለ አንቺም፥ ሰላምን ይናገራሉ።
በየውሃት የሚሄድ ተማምኖ ይኖራል፤ መንገዱን የሚያጣምም ግን ይታወቃል።
የጽድቅን ጎዳና ይጠብቃል፤ የሚፈሩትንም መንገድ ያጸናል።
ብትሄድ ፍለጋህ አይጠፋም፤ በሮጥህም ጊዜ አትሰናከልም።
ስትሄድም ይመራሃል፤ ከአንተም ጋር ይኖር ዘንድ ውሰደው። ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣም ያነጋግርሃል።
አይራቡም፤ አይጠሙምም፤ አይደክሙም፤ አይተኙም፤ የወገባቸውን መታጠቂያ አይፈቱም፤ የጫማቸውም ማዘቢያ አይበጠስም።
ፈረስ በምድረ በዳ እንደሚያልፍ፥ በቀላይ ውስጥ አሳለፋቸው፥ እነርሱም አልደከሙም።
በአምላካቸው በእግዚአብሔር አበረታቸዋለሁ፥ በስሙም ይመካሉ፥ ይላል እግዚአብሔር።