ምሳሌ 24:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰማይ የወጣ፥ የወረደስ ማን ነው? ነፋስንስ በብብቱ የሰበሰበ ማን ነው? ውኃንስ በልብሱ የቋጠረ ማን ነው? የምድርንስ ዳርቻ ሁሉ ያጸና ማን ነው? ይህን ታውቅ እንደ ሆንህ፥ ስሙ ማን ነው? የልጁስ ስም ማን ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም በያለበት እሾኽ በቅሎበታል፤ መሬቱም ዐረም ለብሷል፤ ቅጥሩም ፈራርሷል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም፥ ሁሉ እሾህ ሞልቶበታል፥ ፊቱንም ሳማ ሸፍኖታል፥ የድንጋዩም ቅጥር ፈርሶአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአረምና በቊጥቋጦ ተሞልቶ ነበር፤ በዙሪያውም ያለ የግንብ አጥር ፈርሶአል። |
አሁንም በወይኔ ላይ የማደርገውን እነግራችኋለሁ፤ አጥሩን እነቅላለሁ፤ ለብዝበዛም ይሆናል፤ ቅጥሩንም አፈርሳለሁ፤ ለመራገጫም ይሆናል።
ባድማ አደርገዋለሁ፤ አይገረዝም፤ አይኰተኰትም፤ እንደ ጠፍ ቦታ ኵርንችትና እሾህ ይበቅልበታል፤ ዝናብንም እንዳያዘንቡበት ደመናዎችን አዝዛለሁ።
እግዚአብሔር ለይሁዳ ወንዶችና ለኢየሩሳሌም ነዋሪዎች እንዲህ ይላልና፦ ልባችሁን አድሱ በእሾህም ላይ አትዝሩ።