ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በዕውቀትም ይጸናል።
ቤት በጥበብ ይሠራል፤ በማስተዋልም ይጸናል፤
ቤት በጥበብ ይሠራል፥ በማስተዋልም ይጸናል፥
በጥበብ ቤት ይሠራል፤ በማስተዋልም ጸንቶ እንዲኖር ይደረጋል።
ስምህ ለዘለዓለም ታላቅ ይሁን።
ብልሆች ሴቶች ቤቶችን ይሠራሉ፤ ሰነፎች ሴቶች ግን በእጃቸው ያፈርሳሉ።
ጥበብ ለራስዋ ቤቷን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶዎችዋን አቆመች።
ምድርን በኀይሉ የፈጠረ፥ ዓለሙን በጥበቡ ያጸና፥ ሰማያትንም በማስተዋሉ የዘረጋ እርሱ ነው።
በእግዚአብሔር ሥራ እንተባበራለንና፤ የእግዚአብሔርም አገልጋዮች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።
በእርሱ ተመሥርታችሁ ታነጹ፤ በምስጋናው ትበዙ ዘንድ፥ በተማራችሁት ሃይማኖት ጽኑ።