ንጉሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውን ዘር የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን” አለ።
ምሳሌ 23:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጻድቅ አባት በመልካም ያሳድጋል፥ በብልህ ልጅም ነፍሱ ደስ ይላታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቅ ሰው አባት እጅግ ደስ ይለዋል፤ ጠቢብ ልጅ ያለውም በርሱ ሐሤት ያደርጋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ አባት እጅግ ደስ ይለዋል፥ ጠቢብንም ልጅ የወለደ ሐሤትን ያገኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጨዋ ልጅ አባት ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፤ ብልኅ ልጅ የወለደም ሰው ኲራት ይሰማዋል። |
ንጉሡም፥ “ዐይኔ እያየ ዛሬ በዙፋኔ ላይ የሚቀመጠውን ዘር የሰጠኝ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን” አለ።
አንተ ግን ጥበበኛ ሰው ነህና ንጹሕ አታድርገው፤ የምታደርግበትንም አንተ ታውቃለህ፤ ሽበቱንም በደም ወደ መቃብር አውርደው” አለው።
ጠቢብ ወይም አላዋቂ እንደሚሆን ከፀሐይ በታችም በደከምሁበትና ጠቢብ በሆንሁበት በድካሜ ሁሉ ይሰለጥን እንደ ሆነ የሚያውቅ ሰው ማን ነው? ይህም ደግሞ ከንቱ ነው።